ፕሮግራሞቻችን
ተጨማሪ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለን ፕሮግራም ይምረጡ::
ማህደረመረጃ እና የሕዝብ ግንኙነት
የአማራ ኅብረተሰብ ቅርስ በሚኔሶታ የማህደረመረጃ እና የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የድርጅቱን የማህደረመረጃ እና የሕዝብ ግንኙነት ህግ በጠበቀ መልኩ የውስጥ እና የውጪ የሕዝብ ግንኙነትን ማካሄድ እና የድርጅቱን ዓላማ፣ጥረት እና እንቅስቃሴ የሚያሰራጩ የማስታወቂያ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ሃላፊነት አለው። የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው/ሃላፊዋ የሕዝብ ግንኙነት ዕቅድን ማውጣት፣ ዘዴን መተለም፣ በጀት ማርቀቅ እና ባጠቃላይ ድርጅቱን ለህዝብ የሚያስተዋውቁ ስራዎች ላይ መሳተፍ ሃላፊነቱ/ሃላፊነቷ ነው። በተጨማሪም የድርጅቱ መልዕክቶች ለህዝብ የሚያደርሱ በራሪ ወረቀቶችን እና መልዕክቶችን ማዘጋጀት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው/ሃላፊዋ ስራ ነው። የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው/ሃላፊዋ ዝርዝር ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.9 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የቴክኖሎጂ እና የሙያ አማካሪ
ይህ መርሃ ግብር የዘመኑን ቴክኖሎጂ በሚኔሶታ እና በሚኔሶታ ባሻገር ለሚገኙ አማራዎች በማስተማር እና በማሰልጠን ላይ ያተኩራል። ቴክኖሎጂ እያደገ እና እየዳበረ በመጣ ቁጥር የአማራው ህዝብ በሳይንስ፣ምህንድስና፣ሂሳብ እና ቴክኖሎጂ መስኮች የሚያደርገው ተሳትፎ በህብረተሰቡ ውስጥ ለሚኖረው እድገት ወሳኝ ነው። የቅርቡ ኮፊ አናን እንደተናገሩት “ዕውቀት ሀይል ነው። መረጃ ነጻ ያወጣል። በማንኛውም ቤተሰብ እና ኅብረተሰብ ትምህርት የእድገት መዳረሻ ነው።
ስለዚህ ይህ ድርጅት በአማራው ህዝብ ዘንድ ያለውን የቴክኖሎጂ እና የሙያዊ ምክር የእርዳታ ፍላጎት ለመመለስ በዚህ ዘርፍ በተለያዪ የእድሜ ክልል ላሉ ወገኖች አገልግሎት ለመስጠት በከፍተኛ ስሜት ተዘጋጅቷል። በይበልጥ የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ የአማራ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ፣በማወያየት አና አብሮ በመስራት የአጭር እና የረዥም ጊዜ እቅድ አውጥቶ ወገናችን ከነዚህ ባለሙያዎች ከሚገኘው ዘርፈ ሰፊ የሙያ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆን ይጥራል። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.14 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የዝግጅት ዕቅድ አውጪ እና ገንዘብ አሰባሳቢ
ከስሙ መረዳት እንረሚቻለው ትርፍ አልባ ድርጅቶች ለሚያገለግሉት ህብረተሰብ ከሚሰጧቸው አገልግሎትቶች ትርፍ አያገኙም። ዋነኛው የገቢ ምንጫቸው ከአባላቶቻቸው እና ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች የሚሰጧችው የመርሃ ግብር እና የስራ ማስፈጸሚያ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ስለዚህ እነዚህ ድርጅቶች ስኬታማ፣ ጠንካራ እና ዘላቂ ድርጅት እንዲሆኑ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እና አቅም ግንባታ እንቅስቃሴዎችን በስራ እቅዳቸው ውስጥ በዋነኛነት ማካተት ይኖርባቸዋል።
የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ የዝግጅት ዕቅድ አውጪ እና ገንዘብ አሰባሳቢ ጽህፈት ቤት ድርጅቱ የሚያደርጋቸውን ዝግጅቶች ማቀድ እና ለድርጅቱ ገንዘብ ሊያስገኙ የሚችሉ ዘዴዎችን ለምሳሌ ለጋሾችን እና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ማፈላለግ ዋነኛ ሃላፊነቱ ነው። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.10 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የበጎ ፈቃደኞች አስተባባሪ
በቅርብ ዚዜ ግልጽ እየሆነ የመጣው በበጎ ፈቃደኝነት ነጻ ገልጋሎት ሰጪ ግለሰቦች ከትርፍ ነጻ ለሆኑ ድርጀቶች ትል ዋጋ ያላችው ሃብቶች መሆናቸው ነው። ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በአመት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚገመቱ ገለሰቦች የነጻ አገልግሎት እንደሚሰጡ እና ይህ አገልግሎት በገንዘብ ቢተመን ወደ 150 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚሆን የገመታል። ከለጋሾች ገንዘብ ማሰባሰብ እና ከዓባላት የዓባልነት ከፈያ ማሰከፈል ከትርፍ ነጻ ለሆኑ ድርጀቶች የተለመደ የገንዘብ ማግኛ መንገድ ቢሆንም “ጊዜ ገንዘብ ነው” እንዲሉ እነዚህ ድርጅቶች ከገንዘብ በተጨማሪ በሌላ አይነት መንገድ ደጋፍ የሚሰጡ እጆችን የሻሉ። በጎ ፈቃደኞች ለድርጅቶቹ ገንዘብ ከመቆጠብ በተጨማሪ ለደንበኞቭ የተሻለ አገልገሎት በመስጠት፣ ከማህበረሰቡ ጋር ጥልቅ ገነኙነት በመፍጠር፣ ገንዘብ በማሰባሰብ፣ ሙያዊ አገልግሎት በማቅረብ፣ አስተዳደራዊ እርዳታ በመስጠት እና የድርጅቱን ዓላማ እና ራዕይ በማሰራጭት ያግዛሉ። ስለዚህ በጎ ፈቃደኞች ማሰባበብ እና በሚገባው መልኩ ማስተዳደር ከትርፍ ነጻ ለውስብስብ እና ትኩረትንያሚሻ ተግባር ነው።
የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ የበጎ ፈቃደኞች አስተባባሪ ጽሀፈት ቤት በበጎ ፈቃደኝነት ነጻ ገልጋሎት ሰጪ ግለሰቦች በመመልመል ድርጅቱ ውጤታማ የሆነ የበጎ ፈቃደኞች መርሀ ግብር እንዲኖረው ማድረግ ሃላፊነቱነው። ከሌሎች መርሀ ግብር ሃላፊዎች ጋር አብሮ በመስራት ድርጅት ለሚያቅዳቸው የተለያዩ ስራዎች የሚያስፈልጉ ፍቃደኞችን ከድርጅቱ ዓባላት ወይም ከጠቅላላው ኅብረተሰብ በማፈላለግ ያቀርባል። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.8 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የዓባላት ምልመላ
ትርፍ አልባ ለሆኑ ድርጅቶች ዓባላት የጀርባ አጥንት ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች ከአባሎቻቸው የዓባልነት ክፍያ እና የገንዘብ ልገሳ ተቀብለው በምትኩ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት እና የተሳትፎ መድረኮችን በመፍጠር ከዓባሎቻቸው ጋር ያለውን ገነኙነት የጋራ ጥቅም እንዲኖረው ያደርጋሉ። የድርጅቶቹ የዓባልነት ስርአት ከዓባላቱ የገንዘብ፣የጊዜ እና ሌሎች ተሳትፎዎችን በመጠየቅ በምትኩ ዓባላቱ በድርጅቱ የመወከል እና ከድርጅቱ የተለያዩ አገልግሎቶች በማግኘት በድርጅቱ ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ ግነኙነት ፈጥሮ መቆየትን ያካትታል። ዓባላት ከሌሎች ዓባል ካልሆኑ ግለሰቦች በተለየ ሁኔታ ጥቅማ ጥቅሞችን ሊያገኙ ይችላሉ። እንደድርጅቱ ህግና ደንብ መሰረት ዓባላት የድርጅቱ ዓባል ለመሆን አንዳንድ መስፈርቶችን ማሟላት ሊኖርባቸው ይችላል። ብዛት ያላቸውን ዓባላት መመልመል፣ የነዚህን ዓባላት መረጃ አጠናቅሮ መያዝ እና በቀላሉ ተፈልጎ እንዲገኝ የሚያስችል ዝርዝር መፍጠር ከፍተኛ ጥረትን ይጠይቃል።
የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ የአባላት ምልመላ ጽህፈት ቤት በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ዓባላትን መመልመል እና መረጃቸውን አጠናቅሮ ማስቀመጥ እንዲሁም አዲስ ዓባላትን ስለድርጅቱ ዓላማ እና ራዕይ እና የዓባላትን መብት እና ግዴታ ማስተዋወቅ ሃላፊነቱ ሲሆን ከዚሀ በተጨማሪ ዓባላትን ለመመልመል የሚያስችሉ ዝግጅቶችን እና መድረኮችን ያፈላልጋል። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.11 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የትምህርት፣ ስነ ጥበብ እና ባህል
ባሀልና ቅርስ የአንድ ህብረተሰብን ባሕርይ እና ታሪካዊ ዋጋ ያላቸውን ቁሳቁስትን ያሚያካትት ሲሆን ካለፈው ትውልድ ተወርሶ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ የህብረተሰቡ ሃብት ነው። የአንድ ህብረተሰብ ባሀልና ቅርስ የህብረተሰቡን ቋንቋ፣ ሙዚቃ፣ ባህላዊ ቦታዎችን፣ የጥንት ህንጻዎችን፣ አፈ ታሪኮች፣ ትወናዎች፣ ማህበራዊ ልማዶች፣ አምልኮዎች፣ ክብረ በዓላት፣ ሀውልቶች፣ቅዱስ ስፍራዎች ወዘተርፈ የሚያካትት ባጠቃላይ ማንነቱን የሚገልጽ ልዩ ምልክቱ ነው። ምንም አይነት ቅርስ እና ይዘት ይኑረው ይህን ቅርስ ጠብቆ እና ተንከባክቦ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ያሁኑ ትውልድ ግዴታ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለበት።
የአማራ ኅብረተሰብ ቅርስ በሚኔሶታ ውብ የሆነውን የአማራን ህዝብ ታሪክ፣ባህል እና ቅርስ ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅ፣ ለማስተዋወቅ እና ለማጋራት የተቋቋመ ድርጅት ነው። የዚሀ ድርጅት የትምህርት፣ ስነ ጥበብ እና ባህል ጽሀፈት ቤት የድርጅቱን የትምህርት መርሃ ግብር ለምሳሌ የግእዝ እና የአማርኛ ትምህርት፣ የአማራ የባህል ምግቦች አሰራር ትምህርት፣ የአማራ የባህል ሙዚቃ መሳሪያዎች አጨዋወት ትምህርት እና ሌሎች በኪነ ጥበብ ዘርፍ የታቀዱ ሰራዎችን የመቅረጽ እና የማስተዳደር ሃላፊነት አለው። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.12 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የጤና እና ሁለንተናዊ ደህንነት አገልግሎቶች
ጥሩ ግንዛቤ ያለው የአማራ ኅብረተሰብ በሚኔሶታ ለመፍጠር በምንንቀሳቀስበት ወቅት ጥሩ የጤና አጠባበቅ እና አጠቃላይ ደህንነት በቀዳሚነት የሚነሳ ዓላማችን መሆን ይገባዋል። የመጣንበት የጤና ጥበቃ ባህል ከላይ ወደታች የሆነ፤ ማለትም የጤና ባለሙያው የሚያዘው ሁሉ ያለምንም ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝበት ነው። ነገር ግን ዩኤስ ስንመጣ እራሳችንን በተቀናጀ የጤና ጥበቃ ማለትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በጋራ ለአንድ የተሳካ የጤና እና የደህንነት ወጤት የሚሰሩበት ስርአት ውስጥ እናገኛለን። ታማሚው በጤናው ምርምር፣ ግኝት እና የግኝቱ አጠቃቀም ላይ ዋና ሚና ይጫወታል።
የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ የጤና እና ሁለንተናዊ ደህንነት አገልግሎቶች ቢሮ በሚኔሶታ ሰላለው የጤና ፍላጎት፣ መብቶች እና አገልግሎቶች መረጃ በመስጠት እና በማስተማር የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል። አቅም እና ህግ በሚፈቅደው መጠን የተወሰኑ አገልግሎቶችን በቀጥታ ለህብረተሰሰቡ ለመስጠት ይሞከራል።
ከዚሀ ባላነሰ መልኩ ኢትዮጵያ ባልተመጣጠነ እና እምነት በጎደለው የጤና ጥበቃ ስርአት ውስጥ የሚኖረው አማራው ወገናችንን መርዳት ቀዳሚው ስራችን ነው። ይህ ሊሆን ከቻለበት ምክንያቶች አንዱ መንግስት የጤና አገልግሎትን ከፖለቲካ ጋር በማስተሳሰር ኅብረተሰቡ ባለው የጤና አገልግሎት ተጥቃሚ እንዳይሆን መሰናክሎችን በመፍጠሩ ነው። የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ ባገኘው አጋጣሚዎች እና ባስፈለገ ጌዜ ሁሉ ድምጹን ከማሰማት እና ምክርን ከመለገስ ባሻገር በጤና ጉዳዮች ላይ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን፣የመገልገያ መሳሪያዎችን ሌሎችን ከሚለግሱና ከሚያከፋፍሉ አካላት ጋር በመተባበር ወገኖቹን ይረዳል። ሁሉን በሚያከብር ባህላችን መሰረት ይህን ራዕያችንን ከአማራው ኅበረተሰብ አልፈን ለመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪቃ ለማራዘም እቅዳችን ነው።
የጤና እና ሁለንተናዊ ደህንነት አገልግሎቶች ቢሮ ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.15 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።
የገንዘብ አያያዝ እና አጠቃቀም
አብዛኛው የማህበረሰባችን ዓባላት በአሜሪካ የተረጋጋ ኑሮ ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ የገንዘብ አያያዝ እና አስተዳደር እውቀት የላቸውም። የወር ከወር ወጪን ከመሸፈን ጀምሮ ቤት እስከመግዛት፣ ለችግር ጊዜ ገንዘብ ከመቆጠብ ጀምሮ ለልጆች ኮሌጅ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ እስከማጠራቀም ያሉት ድርጊቶች የገንዘብ እቅድ የማውጣት እና የማስተዳደር እውቅትን ይፈልጋሉ። መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ አብዛኛው የማህበረሰባችን ዓባላት ይህንን እውቀት አንብቦ ለመረዳት የሚያስችል የትምህርት ደረጃ የላቸውም። በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ወስጥ የገንዘብ አስተዳደር እና ሂሳብ አያያዝ ትምህርቶች ቢያስተምሩም የገንዘብ ቁጠባ፣ የወጪ እቅድ፣ የግል ገንዘብ አስተዳደር እና የቀረጥ ስርአቱ እንዴት እንደሚሰራ ስለማያስተምሩ ከ12 ኛ ክፍል ያለፈ ትምህርት ያላቸው እነኳን በዚህ ጉዳይ ላይ ይቸገራሉ።
የአማራ ቅርስ በሚኔሶታ : የገንዘብ አያያዝ እና አጠቃቀም አማካሪ ጽህፈት ቤት በገንዘብ አያያዝ እና አስተዳደር ላይ እውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፈላለግ እና ማህበረሰባችን እነዲያስተምሩ በመጋበዝ በማህበረሰባችን ውስጥ በዚሀ ረገድ ያለውን የእውቀት ክፍተት ለመድፈን የተቻለውን ያደርጋል። የዚህ ጽሀፈት ቤት ስራዎች በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.13 የተዘረዘሩ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ ከድርጅቱ አመራር አካላት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ደርቦ ይሰራል።